በዘመናት መካከል ጠብቆ ያኖረንን ፈጣሪ እግዚአብሔርን የሚያመልከው ዘማሪ ደረጀ ከበደ (ዶ/ር) ለጠቅላይ ሚንስትር አብይ ደብዳቤ ጽፎ በአደባባይ አስነብቧል።
እርግጥ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሁኔታ አሳሳብም ከመሆኑም በላይ አፋጣኝ መፍትሄ ካልተወሰደ እልቂት እያስከተለ ነው። ኦሮሚያ ክልል ተብሎ በሚጠራው ሰፊ የሃገራችን ክፍል የሰው ልጅ ነፍስ ዋጋ ካጣች ሰነባብቷል። በአደባባይ ላይ ሰው ተገድሎ ተሰቅሏል። ቤተክርስትያን ተቃጥሏል። የሰው ልጅ ከነ ነፍሱ በቤቱ ውስጥ ተቃጥሏል። እርጉዝ ሴት ሆዷ ውስጥ ካለው ልጇ ጋር በዘጠኝ ወር ጊዜዋ ታርዳለች።
መከራና ስቃይ የበዛበት የኢትዮጵያ ህዝብ አሁንም፣ ዛሬም አማራ ወይም ክርስትያን በመሆኑ ብቻ የሰው ልጅ በኦሮሚያ ክልል እየሞተ ነው።
መንግስት ለዚህ ሁሉ አደጋ ከውጭ ሃይል ጋር የሚሰሩ ቡድኖች ያሉትን እያሰረ መሆኑ ይታወቃል። የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚፈጽሙትን ለማስቆም ያለው ቁርጠኝነት የሚደነቅ ብሆንም የህይወት አድን እና የታርካችን ከባው ውሳኔ የሚያስፈልግ መሆኑ ግልፅ ነው።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዶ/ር ደረጀ ከባደ በመራር ቃላቶች ለክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ መልዕክት አስተላልፏል። ሙሉውን ተከታተሉ። (Video for Ethio- 360 Media )
- Blue Flowers Under Open Skies: Finding Courage in the Colors of Hope
- Among the Olive Groves: What Ancient Trees Teach About Endurance
- The Almond Blossom of Jerusalem: Hope That Arrives Before Spring
- The Olive Tree and the Rose: A Floral Reflection on the Resilience of Israel
- A Thousand Petals of Gratitude: Learning to Notice Everyday Beauty
